ወንድሞች

 


ለዚህ ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ የተመደቡ የቅዱስ ዮሐንስ ማኅበር ወንድሞች 5 ሲሆኑ።


  1. Puceአባ አትናቲዮስ (የማኅበር አለቃ)

  2. Puceአባ ቤኔዲክቶስ ዳዊት

  3. Puceአባ ፊሊፖስ (የወጣቶች መሪ ካህን)

  4. Puceወንድም ኤርምያስ

  5. Puceወንድም ያዕቆብ

  6. Puceወንድም ዮሐንስ

  7. Puceወንድም አልዓዛር


ከቅዱስ ዮሐንስ ወንድሞች የሕይወት መመሪያ ውስጥ ጥቂት ነጥቦችን ለመጥቀስ፦


የቅዱስ ዮሐንስ ማኅበር ወንድሞች የእግዚአብሔር ልጆችና የኢየሱስ የቅርብ ጓደኞች በመሆን በመንፈስ ቅዱስ አንድነት ሙሉ በሙሉ ክርስቶስን በመከተል ለመኖር የሚሹ ናቸው፡፡


የኢየሱስን ሐዋርያዊ ሕይወት ለመከተል፤ በፍፁም ፀጥታ፣ በቅዱስ ቁርባን ስግደትና ጥልቅ በሆነ የክርስቶስ ሚስጥራዊ ሕይወት አስተንትኖ በማድረግ ከማርያም ጋር የጠበቀ ሕብረት እንዲኖር የማኅበሩ አባላት በፀሎት ይተጋሉ፡፡


የቅዱስ ዮሐንስ ማኅበር እነማን ናቸው?


የቅዱስ ዮሐንስ ማኅበር ሕዳር 28 ቀን 1968 ዓ. ም. በአባ ማሪ ዶሚኒክ ፊሊፕ ተመሠረተ፡፡ በጳጳስ አውተን (በርጀንዲ፣ ፈረንሣይ) እንደ ሰበካ ማኅበር መርህ በ1979 እውቅናውንም አገኘ፡፡ ዛሬ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች 61 ገዳማት አሉት፡፡


የቅዱስ ዮሐንስ ማኅበር አባላት በዮሐንስ ወንጌል በተገለጡት ሦስቱ የቃልኪዳን መሠረቶች በስብከተ ወንጌል አገልግሎት መኖር ይፈልጋሉ፡፡ እነሱም፦


1.በቅዱስ ቁርባን ውስጥ ካለው ኢየሱስ ጋር ያለው ቃልኪዳን፡- ይህ በጽሞና በሚደረግ የቅዱስ ቁርባን ስግደትና የቅዳሴ ሥርዓተ አምልኮ ሚስጥራዊ ከመሆኑ የተነሣ ማኅበሩ በተቻለው መጠን የጸጥታን ሕይወት በማዋኃድ ለመኖር ይጥራል፡፡ ነገር ግን ከሐዋርያዊ ሕይወት ከሚጠበቀው ኃላፊነት አንፃር ሰፊ ጊዜን ለፅሞና ፀሎት መስጠትን ይፈልጋል፡፡


2.ከማርያም ጋር ባለው ቃልኪዳን ፡- እናትም የእምነት እድገት ጠባቂ፣ ተስፋና ፍቅር ከሆነች ማርያም ጋር በአስተንትኖ በመትጋት መለኮታዊ የሆነውን ሕይወት በጥልቅ ማሰብ ነው፡፡ በዮሐንስ ወንጌል 19፡17 ላይ እንደተጻፈው «ከዚህ ጀምሮ ደቀመዝሙሩ ወደ ቤት ወሰዳት» እንደሚለው እንዲሁ በገዳሙ ለሚኖሩ ወንድሞች የወንድማማችነትና የፍቅር መሠረት ነው፡፡


3.እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ ሰው ከጴጥሮስ ጋር ያለ ቃልኪዳን፡- የልጅነት ተዓዝዞን በሚመስል ተዓዝዞ ለቤተክርስቲያን መሪዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትና ጳጳሳት ለቤተክርስቲያን ትምህርት መታዘዝን ያመለክታል፡፡ ይህንን በማድረግ ወንድሞች በሙሉ ሕይወታቸውን በመስጠት በብርሃን ውስጥ መመላለስ «በእውነት ቀድሳቸው» ተብሎ በዮሐንስ ወንጌል 17፡17 ላይ ኢየሱስ ለሐዋርያቶቹ አባቱን እንደጠየቀና ወደ ዓለም እንደላክኸኝ እንዲሁ እኔ ወደ ዓለም ላክኋቸው እነሱም ደግሞ በእውነት የተቀደሱ እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነሱ እቀድሳለሁ» ዮሐ. 17 ፡17-19 እንደሚል፡፡


እንደ ዮሐንስ በፍቅር ታማኝ ምስክር በመሆን ሙሉ በሙሉ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት እያንዳንዱ በጥልቀትና በበቂ ማስተዋል እንዲሞላ አስፈላጊው ትምህርት እንዲሰጠው ያስፈልጋል፡፡ ይህ ትሕትና የተሞላበት እውነትን ፍለጋ፣ አስተሳሰብን፣ ማስተዋልንና መንፈሳዊ ሕይወትን መቀየር የሚያስችል ነው፡፡


ይህም የመንፃት ሕይወት ፍፁም የሆነ ፍቅርና ነፃነት ወደ ክርስቶስ የበለጠ እንድንቀርብ ይረዳናል፡፡ ይህም በዮሐንስ ወንጌል 3፡21 «እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጊ እንደሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል» እንደሚል ይህም በማህበሩ አባላት ሕይወት ተፈፃሚ እንዲሆን ይረዳል፡፡

የቅዱስ ዮሐንስ ማኅበር ወንድሞችWelcome to :


ወደ OUR BLOG


ወደ OUR NEWSLETTER Download :


ወደ የቀን መቁጥሪያ

Access plan:

Please download the access plan on the following link.