ስለ ገዳሙ

 


የቅዱስ ዮሐንስ ማኅበር ገዳም በመሐል አዲስ አበባ፣ እንግሊዝ ኤምባሲ አካባቢ ከSchool of tomorrow ምልክት ወረድ ብሎ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይህም ቀድሞ ለአረጋውያን ካህናት መጦሪያ ሆኖ ያገለግል ነበር፡፡ ሰበካውም ይህንን ቤት በኃላፊነት ማህበሩ የራሱን መሬት አግኝቶ ገዳም እስኪሰራ እንዲጠቀምበት ፈቅዷል፡፡


ቤቱ አስቀድሞ በብፁዕ አባ ገ/ሚካኤል ጠባቂነት ስር የነበረ ሲሆን፣ ብፁዕ አባ ገ/ሚካኤል ሰማዕት ሆነው ያለፉ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ፤ በጎጃም አካባቢ ተወልደው እድሜአቸው ለእውቀት እንደደረሰም እውነትን ፍለጋ በሚጥሩበት ጊዜ ቅዱስ ጎስቲኖ ደ ጃኮቢስ በመንገዳቸው ላይ ያገኛሉ፡፡ በእርሳቸውም እርዳታ ወደ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ይመጣሉ፡፡


ከመጡም በኋላ ለረጅም ዘመን ሕይወታቸው መስዋዕት በማድረግ በሐምሌ 7 ቀን 1847 ዓ. ም. በሰባ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ከሞታቸው በኋላም ብዙ ቁጥር ያላቸው መንፈሳዊ ማኅበራት የጨመሩና ስማቸውንም እንደ ማኅበር መጠሪያ ይጠቀሙበት ጀመር፡፡


በገዳሙ የፀሎት ሰዓት ለመሳተፍ ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው በራችን ክፍት ነው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ወንድሞች የጸሎት ሰዓት ከዚህ ቀጥሎ ማግኘት ይችላሉ፡፡


ክፍት የሚሆንባቸው ቀናት፡-


 1. Puceበሣምንት ቀናት (ከሰኞ - አርብ)

 2.         12.00    የማታ ጸሎት

 3.         12.30    ቅዳሴ

 4.         1.00     የቅዱስ ቁርባን ስግደት


 5. Puceሀሙስ

 6.         11.30          ቅዳሴ በፈረንሳይኛ (Holy Savior)

 7.         12.30 - 2.30   የቅዱስ ቁርባን ስግደት 8. Puceቀዳሜ

 9.         2.00    ቅዳሴ


 10. Puceእሁድ

 11.         11.30    የማታ ጸሎት

 12.         12.00    የቅዱስ ቁርባን ስግደትAccess Map :


የብፁዕ አባ ገ/ሚካኤል ቤት አቅጣጫን download ለማድረግ ከታች ይጫኑ፡

የብፁዕ አባ ገ/ሚካኤል ቤትWelcome to :


ወደ OUR BLOG

ወደ OUR NEWSLETTER


Download :


ወደ የቀን መቁጥሪያ